ለኢትዮጵያ እና ኬንያ ቁልፍ የንግድ ከተማ የሆነችው ሞያሌ ዳግም በግጭት ስትናጥ ወደ 50,000 የሚሆኑ ሰዎች ተሰደዋል። ሞያሌ የሰዎች፣ የአደንዛዥ እጽ እና የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች የሚያዘወትሯት ኹነኛ የገበያ ማዕከል ነች። የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች በይገባኛል የሚወዛገቡባት ከተማ የግጭት ሰለባ ስትሆን የአሁኑ የመጀመሪያ አይደለም።