የሞያሌውን ግጭት አለመረጋጋት ተከትሎ ወደ ኬንያ ብቻ የተፈናቀሉት ከ50 ሺህ በላይ መሆኑን የዓለማቀፍ የመብት እና የሰብዓዊ ተቋማት እየገለጹ ነው።

Wait 5 sec.

በኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ ሞያሌ ከተማ ውስጥ በተከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት የተፈጠረው ሰብዓዊ ቀውስ ሊቆም እንደሚገባው ተጠየቀ። አስተያየታቸውን ከተለያዩ አከባቢዎች ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ኢትዮጵያውያን እንዳሉት በግጭቱ ዙሪያ በመንግስት በኩል በቂ ማብራሪያ እና የምፍተሄ አቅጣጫ ለህዝቡ አለመሰጠቱ የሚነቀፍ ተግባር ነው ።