ከተጀመረ 16ኛ ቀኑን የያዘውን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤን የተመለከቱ መረጃዎች በየጊዜው በኮሚሽኑ የበላይ ኃላፊዎች ይሰጣሉ። የውይይቶች ድባብ ምን እንደሚመስል በቀጥታ ለሕዝብ እየቀረበ ግን አይደለም። አንዳዶች የጉባኤው ውሎ በቀጥታ እንዲሰራጭ ወይም በውይይት ሂደቱ ስለሚነሱ ጭብጦች ተጨማሪ መረጃዎች ለሕዝብ እንዲደርስ ቢደረግ ይመርጣሉ።