በአገራዊ ምክክር ሂደቱ እየተሳተፉ የሚገኙ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክክር ሂደቱ ላይ አለን ያሉትን ሥጋት ገለፁ። ፓርቲዎቹ ለምክክሩ ስኬት ጥሪ፣ ለኮሚሽኑ ማሳሰቢያ እና የአካሄድ እርምት በጠየቁበት መግለጫቸው «የአንድ ወገን ፍላጎትን በሌሎች ላይ ለመጫን» የሚደረግ ያሉት ጥረት ሥጋት እንደፈጠረባቸው ጠቅሰዋል።