ውጊያ ተካሄደ ከተባለበት ከሸረሪና አካባቢ ቁስለኞችን ጨምሮ ሌሎችም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ሱዳን መግባታቸውን የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል። ከውጊያው በኋላ የትግራይ ተዋጊዎች ናቸው የተባሉ አስከሬኖች ሱዳን ድንበር ላይ መገኘታቸውንም የህክምና ምንጮች መናገራቸውም ተዘግቧል።