የኬንያ ፕሬዝዳንት የፓርላማ አባላቱን ጉቦ እየተቀበሉ ነው ብለው በጅምላ ከወቀሱ ወዲህ፤ የኬንያን ፖለቲከኞችን እያወዛገበ ነው። በሀገሪቱ የተደረገ አዲስ ጥናት እንዳመለከተው ዜጎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ብቻ ጎቦ ለመስጠት ይገደዳሉ። በኬንያ በየዓመቱ ወደ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ከዝርፊያ እና ከህገወጥ የገንዘብ ፍሰት እንሚጠፋ ይገመታል።