በራያ አላማጣ ወረዳ መርዋ በተሰኘች አካባቢ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ተሰብስበው በነበሩ የህወሓት ታጣቂዎች ላይ ትናንት ሐምሌ 4 ቀን፣ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ ። በጥቃቱ በርካታ ሰዎች ሳይጎዱ እንዳልቀረና ጉዳተኞች ወደ አላማጣ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል ።