ራሱን፣ ቤተሰብ፣ ዘመድ ወዳጅ፣ ሕዝብ ሐገሩን ሊጠቅም የሚችል በሺሕ የሚቆጠር ወጣት ረገፏል።ብዙ ሺዎች እጅ-እግር፣ አይን-ሌላ አካላቸዉን አጥተዋል።አርሶ ማምረት፣ ሰርቶ ማፍራት የሚችል ጎልማሳ፣ በየመጠለያ ጣቢያዉ ተማፅዋች ሆኗል።የመብት ተሟጋቾች እንዳሉት ልጃገረድ-ከባለ ትዳር ሳትለይ ተደፍራለች።