የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ በፊት በኤርትራ መንግስት ተይዞብኛል ያለው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እስካሁንም አለመለቀቁን ዐሳወቀ፡፡ በ2018 በጀት ዓመት 9.1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱንም ይፋ አድርጓል ። በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተው ግጭት ለአየር መንገዱ ትልቁ ፈተና ሆኖ ማለፉም ተጠቅሷል ።