በትግራይ ክልል በሚገኙ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጣቢያዎች ላይ የሚቀርቡ እርዳታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ መምጣቱን ተፈናቃዮቹ እየገለጹ ነው፡፡ እንደ ተፈናቃዮቹ፤ በየወሩ ይቀርብ የነበረው የእርዳታ አቅርቦት አሁን አሁን አልፎ አልፎ ብቻ ሳይሆን መጠኑም እየቀነሰ መምጣቱ እና ህይወታቸዉን ስከፊ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል፡፡