የወይንሸት መጠለያ ካምፕ ነዋሪ አቶ መካሻ ይመር ለሁለት ወር ከ10 ቀናት ምንም ዓይነት ምግብ እንዳልቀረበላቸው ይገልጻሉ። «ቀኑም ሌሊቱም፣ ጨለማ ነው ለእኛ። ምንግዜም ሌሊቱም ቀኑም ጨልሞብናል፤ መቼ እንደሚነጋ ብቻ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው። ዝናቡ 24 ሰዓት ነው የሚዘንብብን እንደማንም ብርዱ ይቻል ነበር፤ ግን ረሃብ አይቻልም። »ብለዋል,