የአውሮጳ ኅብረት ፓርላማ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ካጸደቃቸው በኅብረቱ የተገን አሰጣጥ ስርዓት ላይ ከተደረጉት ለውጦች ውስጥ የስደተኞች ተገን ጥያቄ ማመልከቻዎቻቸው ሳይታዩ፣ ወደ ሌላ ሦስተኛ ሀገር እንዲላኩ ማድረግ የሚያስችለው አሰራር በዋነኛነት ይጠቀሳል። ፓርላማው ያጸደቀው ለውጥና አተገባበሩ ከእስካሁኑ በጣም የተለየ ነው።