በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት አላማጣ ግንባር ከቆቦ እስከ ኩኩፍቶ 96 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

Wait 5 sec.

ከባድ ውጊያ እየተደረገበት በሚገኘው የአላማጣ ግንባር ከቆቦ እስከ ኩኩፍቱ 96 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቸ ቬለ ተናገሩ። በአላማጣ ከተማ ብቻ 52 ሰዎች ተገድለዋል። ከከባድ መሣሪያ ለመሸሽ የሞከሩ አምስት ሕጻናት አፉኝት የተባለ ወንዝ ወስዷቸው ህይወታቸውን አጥተዋል።