ምንም እንኳን የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከሕግ በላይ ሆነው በስደተኞች ላይ እርምጃ የሚወስዱትን እነዚህን የተደራጁ ቡድኖች ባለሥልጣኖቻቸው እንደማይታገሱ ባለፈው እሁድ ቢያሳስቡም የተቃውሞ ሰልፎችን ማካሄዳቸው ስደተኞችን ማጥቃት መዝረፋቸው ቀጠለ እንጂ አልቆመም ሲሉ ደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።