የጤና ባለሞያዎች ጥያቄዎች ትኩረት እንዲሰጣቸውና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ ኢሰመኮ አሳሰበ

Wait 5 sec.

በጤና ባለሞያዎች የቀጠለው የሥራ ማቆም አድማ እና በመንግሥት የሚወሰዱ ርምጃዎች አፋጣኝ መፍትኄ ሊያገኙ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ። ችግሩ በመቀራረብ እና በመነጋገር ሊፈታ ይገባል ያለው ኢሰመኮ ፖሊስ የሕክምና ባለሞያዎችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ መሆኑን መገንዘቡንም ዐሳውቋል።