የመንግሥት ኃይሎች ከፋኖና ኦነግ ሸኔ ጋር በሚያካሂደዉ ግጭት ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ በዜጎች ላይ "ግድያ እና የአካል ጉዳት" መፈፀማቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አታወቀ። ኮሚሽኑ ከሰኔ 2016 እስካ ሰኔ 2017 ዓ.ም ያለውን ሀገራዊ የሰብዓዊ መብቶች ኹኔታ ሪፖርት ዛሬ ይፋ ሲያደርግ በኦነግ ሸኔ የሚፈፀም እገታ መቀጠሉን ገልጿል።