ኢትዮጵያ ውስጥ የጋራ የሚያስተሳስሩ እሴቶች እየተሸረሸሩ መምጣት ለሰብአዊ መብት ጥሰቶች ምክንያት ናቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ዋና ኮሚሽነር ተናገሩ ። ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፦ መንግሥት ሕገ መንግሥቱን እና የፈረማቸውን ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ሊያከብር እና ሊያስከብር ይገባል ብለዋል ።