በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ድሮንን ጨምሮ በሚጣሉ ከባባድ መሳሪያዎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ የአከባቢው ነዋሪዎች በተለይም ሰኞ እለት በተጣለው ጥቃት ንጹሃን መጎዳታቸውን ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ዛሬ ኦሮሚያ ውስጥ በተለያዩ ዞኖች እና ከተሞች ስለሰላም የሚጣሩ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡