በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ስምንት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ሀገራዊ ምክክር እንዲከናወን የሚያግዝ ጥምረት መመስረታቸውን ገለፁ። ፓርቲዎቹ ይህንን ስምምነታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማስገባታቸውንም ከተጣማሪዎች አንዱ የሆነው ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ለዶቼ ቬለ አረጋግጧል።