የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል "አስቻይ ኹኔታ እስኪፈጠር" የክልሉን አጀንዳ የማሰባሰብ እና የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች ልየታን በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ነው።ኮሚሽኑ ይህንን ሥራ በቀጣዩ ሳምንት የሚያካሂድ ሲሆን፣ በምክክሩ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙና ከክልሉ ይመጣሉ ተብሎ የሚጠበቁ 400 ሰዎች እንደሚሳተፉ ገልጿል።