በርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰው ሱዳን አፋጣኝ የምግብ ርዳታ ባፋጣኝ ካልቀረበ ክምችቱ የፊታችን መጋቢት ወር ማገባደጃ ላይ ሊሟጠጥ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አድርጓል የተመድ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ፎልከር ቱይርክ ሱዳን ውስጥ ከ50 በላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አወያይተዋል ።