ህወሓት በትግራይ ክልል «ምን ዓይነት ሥርዓት ይኑር» በሚለው ላይ ሰሞኑን ውይይት እየተደረገ መሆኑን ለዶቼ ቬለ ገለፀ። ድርጅቱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሥልጣን በፌዴራል መንግሥት «የተናጠል» ያለው ውሳኔ መራዘሙ የፕሪቶሪያን ስምምነት አፍርሶታል በሚል ነው ይህን እያደረገ ያለው።