የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ፕሪቶሪያ ውስጥ የፈረሙትን ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት "አደጋ ላይ የሚጥሉ ማናቸዉም 'ርምጃዎች በአስቸኳይ እንዲረግቡ" የአውሮጳ ሕብረት ጥሪ አቀረበ።ሕብረቱ "ሌላ አዉዳሚ ግጭትን ማስወገድ" እንደሚገባ እና በስምምነቱ ፈራሚዎች መካከል ያሉ "ልዩነቶች በፖለቲካዊ ዉይይት መፈታት" እንዳለባቸው አሳስቧል።