በጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የሚደርሱ እስርና ወከባዎች በኢትዮጵያ በቋፍ ላይ የነበረውን የፕረስ ነጻነት አደጋ ላይ እንደጣለው የሙያው ባለቤቶችና ተከራካሪዎች በየጊዜው ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኝሉ። በሙያው የተሰማሩ ጋዜጠኞች የሙያዊ ክህሎትና የሥነምግባር ችግሮች እንደሚስተዋሉም በመስኩ የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ።