የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና ህወሓት ከምርጫ በፊት ፖለቲካዊ ውይይት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀረበ

Wait 5 sec.

በኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ከምርጫ በፊት ፖለቲካዊ ውይይት እንዲጀመር የአውሮፓ ኅብረት እና የኅብረቱ አባል ሀገራት ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ የሚገኘው የአውሮፓ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ ጥሪውን ያቀረበው ግጭት የማቆም ሥምምነት የተፈረመበትን ሦስተኛ ዓመት በማስመልከት በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው።