«ሕዝብ ለመብቱ በአንድነት መቆም እንዲጀምር» ኢሕአፓ ጥሪ አደረገ

Wait 5 sec.

በገዥው ፓርቲ ይስተዋላል ያለው «ጦረኝነትና ማን አለብኝነት ኢትዮጵያን የመፍረስ አደጋ እንዲጋረጥባት» ማድረጉን የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ከሰሰ ። ፓርቲው 11ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ካከናወነ በኋላ ባወጣው መግለጫ የመንግሥት አካሄድ "ኢትዮጵያውያን የዜግነትና የሰውነት ክብራቸው እንዲገፈፍ ምክንያት ሆኗል" ሲል እርምት ጠይቋል ።