የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ሲፌፓ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የተላለፈበትን ውሳኔ ተቃወመ ፡፡ ፓርቲው ተቃውሞውን ያሰማው በምርጫው ለመሳተፍ ያቀረበው ጥያቄ የቦርዱን ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን ተከትሎ ነው ፡፡