ሰማዩ ደመናን ሲነሳ፣ ምድር ስትደርቅና የሰው ልጅ አቅም ሲዝል፤ የወሎ እናቶች የሚያምኑበት 'እርፎ መረባ'። የሚባል ጽኑ መሸሸጊያ አላቸው። እምነት፣ ዘር እና ቀለም ሳይለያቸው፣ በጋራ ቆመው ወደ ፈጣሪ የሚጮኹበት፣ ጭንቃቸውን አውጥተው ሰላምንና ዝናብን የሚለምኑበትም ነው 'እርፎ መረባ'።