ኢትዮጵያ የባሕር በር "መልሳ የምታገኝበት ጊዜው አሁን ነው" ሲሉ የመከላከያ ሠራዊት የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ ተናገሩ። ይህ የከፍተኛ የጦር መኮንኑ ንግግር በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው የተላለፈ ሲሆን "ይሄ ነገር" ያሉት የባሕር በር "እጃችን ላይ ይገባል" ብለዋል።