ኢራን ቀይ ባሕርን ልትዘጋ እንደምንችል ማስጠንቀቂያ መስጠቷ፣ በአፍሪካ ቀንድና በተቀረውም የአህጉሪቱ አካባቢ የበለጠ ስጋት ደቅኗል። ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኝ እንዳሉት፣የቀጠለው ውጥረት እንዲረግብና ኢኮኖሚያዊ ጫናው እንዲቀንስ፣ አፍሪካ ከሚመለከታቸው ጋር በቅንጅት መስራትና ለተያዘው የሰላም ጥረት ድጋፍ መስጠት አለባት።