በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያሉ የምክር ቤት አባላት፣ ፖለቲከኞች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እና ሌሎችም ከእሥር ሊፈቱ ነው የሚል መረጃ እየተሰራጨ ነው። የዚህን ተጨባጭነት የጠየቅናቸው ከተከሳሽ ጠበቆች አንደኛው መረጃው በስፋት እየተነገረ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን «እስካሁን የተፈታ እሥረኛ የለም» ብለዋል።