ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ይፋ ባደረገው መረጃ በጥቅምት ከኢትዮጵያ የሚነሱ ድንበር የመሻገር እንቅስቃሴዎች 26 በመቶ ጭማሪ እንዳሳዩ ገልጿል። እንቅስቃሴዎቹ በሱዳን፣ በጅቡቲ እና በሶማሊያ በኩል መመዝገባቸውን የጠቀሰው ድርጅቱ የኢኮኖሚ ጫናዎችና በግጭቶች እየጨመረ የመጣው የሰብአዊና የጥበቃ ሥጋቶች ዋና ዋና እንደሆኑ ጠቅሷል።