ስደተኞችን ከመስጠም አደጋ የሚታደጉ የባሕር ላይ ነፍስ አድን ድርጅቶች የማንቂያ ደውሉን እያሰሙ ነው ። በርካታ ሕጻናት እና ወጣቶች በዓለም ላይ ካሉ አደገኛ የስደት መስመሮች አንዱ የሆነውን የሜዲትራኒያንን ባሕር አቋርጠው እየፈለሱ ነው ። በባሕር ከመስጠም ከተረፉት መካከል አንድ አምስተኛው የሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች ናቸው ።