ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በየመን ስደተኞች የተገደሉበት የአሜሪካ ጥቃት “እንደ የጦር ወንጀል” እንዲመረመር አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ

Wait 5 sec.

አሜሪካ በየመን ሳዓዳ እስር ቤት ላይ የፈጸመችው ጥቃት “የሰብአዊ ሕግን የጣሰ” በመሆኑ “እንደ የጦር ወንጀል እንዲመረመር” አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ። ከ100 እስከ 120 ኢትዮጵያውያን በነበሩበት እስር ቤት ላይ በተፈጸመው ጥቃት በርካታ ስደተኞች ተገድለዋል። በሕይወት ከተረፉት ውስጥ ዐይን፣ እጅ እና እግራቸውን ያጡ ይገኙበታል።