በኢትዮጵያ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት እና በሰዎች የመነገድ ወንጄል ሰፊ እና ውስብስብ ችግር መሆኑን በዘርፉ የሚሰሩ ዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ተቋማት ይገልፃሉ።ይህ ችግርም በተለይም ወጣቶችን ሰለባ እያደረገ ሲሆን ፤አንድ ገለልተኛ ዘገባ እንዳመከተው በጅቡቲ በኩል በአማካይ 12,000 ኢትዮጵያውያን በየወሩ ወደ ሳውዲ አረቢያ ይጓዛሉ።