በኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች አዋሳኝ አከባቢ በሚገኘው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ አይመለል ቀበሌ ከኦሮሚያ ክልል ወደ አከባቢ የተንቀሳቀሱ ሸማቂ ታጣቂዎች በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ገለፁ። ደጋግሟል ያሉት ይህ የታጣቂዎቹ ጥቃት መረጋጋት እየነሳቸው በመሆኑ መፍትሄ እንዲያገኝም ጠይቀዋል፡፡