ኤርትራና ሕወሓት ኢትዮጵያን ለመውጋት እየተዘጋጁ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሰ

Wait 5 sec.

የኤርትራ መንግሥት እና ሕወሓት "ፅምዶ" ብለው በጠሩት ሕብረት "በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ለመክፈት በዝግጅት ላይ ናቸው" ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ በጻፈው ደብዳቤ ከሷል። ደብዳቤው እነዚህ አካላት "እንደ ፋኖ ያሉ የታጠቁ ቡድኖችን በገንዘብ እየደገፉ፣ እያስተባበሩ እና እየመሩ ይገኛሉ" ሲልም ይወቅሳል።