ኢትዮጵያ ውስጥ ማርበርግ የተሰኘው ተሐዋሲ መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር አረጋግጧል። በዚህ ምክንያትም የሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል። ማርበርግ ተሐዋሲ የኤቦላ ተሐዋሲ ቤተሰብ ከሚባሉት አደገኛና ለሞት ከሚያደርሱ ተሐዋሲያን አንዱ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።