ዶይቸ ቬለ (DW) ሁለት ዘጋቢዎቹ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በቋሚነት መታገዳቸውን አጥብቆ ይቃወማል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን (EMA) ለዶይቸ ቬለ በጻፈው ደብዳቤ ከጋዜጠኞቹ ዘገባ ጋር በተያያዘ ተጨባጭ ምክንያት አልሰጠም።