ትራምፕ «ከሦስተኛ ዓለም ለሚመጡ ዜጎች ጥገኝነት ተቋርጧል» አሉ

Wait 5 sec.

ዩናይትድ ስቴትስ ከሦስተኛ ዓለም ሀገራት ስደተኞችን መቀበል ማቆምዋን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ። ይህ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተያየት የተሰማዉ አንድ አፍጋናዊ ሁለት የአሜሪካ ብሔራዊ ዘቦች ላይ ተኩስ ከፍቶ ካቆሰላቸዉ በኋላ ነዉ። ከኤርትራ፣ ከሶማልያ፣ ሊቢያና የመንን ጨምሮ ከ 19 ሃገራት ስደተኞች የመኖርያ ፈቃዳቸዉ ይመረመራል ተብሏል።