ከ20 በላይ ሀገራዊ እና ከ40 በላይ ክልላዊ ፓርቲዎች ይሳተፉበታል የተባለው ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የአንድ ወር ጊዜ ነው የቀረው። ቦርዱ በስድስት ክልሎች «የፀጥታ እና አስቻይ የፖለቲካ ምህዳር»ን እንዲገመግም ያደራጀውን ቡድን ማሰማራቱን ባለፈው ሳምንት አስታውቋል።