በጋና እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል የተፈጠረውን የጤና መረጃ ልውውጥ ያስከተለው ውዝግብ ዐበይት መነጋገሪያ ከነበሩ ሰሞንኛ አፍሪቃዊ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነበር። የጤና መረጃዎችን ስለማጋራት የተፈጠረው ስጋት፣ የጋና ባለስልጣናት ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረበችውን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያወጣ የጤና ስምምነት እንዲተዉ እንዳደረጋቸው ተዘግቧል።