በኢትዮጵያ ዉስጥ ስድስት ጋዜጠኞች ታስረዋል። ሁለት የዶይቼ ቬለ DW ዘጋቢዎች በቋሚነት ከስራ ታግደዋል። ሌሎች በፕሪስ ነጻነት ላይ የጭቆና ድርጊቶችን አይተናል። ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰዉን ማስፈራሪያና ሌሎች ነገሮችን ዘግበናል። ጋዜጠኞች ለባለሥልጣን የማይመቹ ወይም ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን ሲናገሩ በሰፊው የጥቃት ኢላማ አካል ሆነዉ እያየን ነዉ።