አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ከተገደሉ በኋላ ኢራን ሦስት አባላት ያሉት የሽግግር ምክር ቤት ሀገሪቱን በጊዜያዊነት እንዲመራ ማዋቀሯን ይፋ አደረገች። ላለፉት 37 ገደማ ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት የ86 ዓመቱ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ፓክፖር እና የሀገሪቱ መከላከያ ምክር ቤት ጸሀፊ አሊ ሻምክኻኒ ተገድለዋል።