ሰሞኑን በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ውስጥ ባሉ ከተሞች ንፁሓን ዜጎች በድሮን ጥቃት መገደላቸውን ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተባለው የአራት ፓርቲዎች ቅንጅት ገለፀ። ቅንጅቱ በዚሁ ክልል "ተፋላሚ ኃይሎች" የአገልግሎት ተቋሟትን ማውደምን ጨምሮ ተደጋጋሚ እገታዎች መፈጸማቸውን ጠቅሶ ድርጊቶቹን አዉግዟል።