ኢትዮጵያ ውስጥ በሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ከባድ ጥሰቶች፣ ግድያ፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ጾታዊ ጥቃት፣ ጠለፋ እና የሰብአዊ አቅርቦት መከልከል አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መብቶች ኮሚቴ ገለፀ። ኮሚቴው መሰል ከባድ ጥሰቶችን ለማቆምና ለመከላከል ኢትዮጵያ ተግባራዊ መሆን የሚገባውን ዓለም አቀፍ ሕግ እንድታከብር አሳስቧል